RSS

Category Archives: NEWS

የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ

ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንበት-7 ጋር ተባብሮ  ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ  የትህዴን አ ባላት የጉንበት-7 አ መራር ከአ ባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አ ጠናክረን እጅ ለእጅ
ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን  የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣ በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አ ያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ
ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በAፈሙዝ ረግጦ ስልጣን  የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የእህAዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አ ምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ እግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች Aባላትና ደጋፊዎች የIህአ ዴግ ስርዓት መለያ ከሆነው በዘር የመከፋፈል Aባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣ የግንበት-7 አመራርናአ ባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው Aስተማማኝ ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አ ብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበትአለን ሲሉ ገልፇል::

 
Leave a comment

Posted by on October 5, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , , , , , , , , ,

የተቃዋሚዎች የሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ከቀጠለ እንደሚቆም ገለጹ!

‹‹በኢሕአዴግ ውስጥ መከፋፈል አለ የተባለው ምኞት ነው››  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

የሃይማኖት አክራሪነት ትግል ፖለቲካዊ ነው አሉ

-የተቃዋሚዎች የሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ከቀጠለ እንደሚቆም ገለጹ

-በኬንያ የደረሰው ጥቃት በኢትዮጵያ ላይ እንደደረሰ ይሰማናል ብለዋል

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ በ2005 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ በይፋ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ቆይታ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታቸው ከተቆጠረ ሁለት ሳምንታት በኋላ ባለፈው ዓርብ ለአገር ውስጥና ለውጭ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ይህ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ወደ ሥልጣን የመጡበትን አንደኛ ዓመት ለማስታወስ ባይሆንም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም በአኅጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በዋናነት ካነሷቸው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዋነኞቹ በኢትዮጵያ የሃይማኖት አክራሪነትና ሽብርተኝነት፣ በኢሕአዴግ ውስጥ አለ ስለሚባለው አለመግባባትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሠልፍ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡ በኢኮኖሚ ረገድ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው ዓመትም ፈጣን ዕድገት ማስመዝገቡን፣ የግል ባለሀብቶች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች ለመሳተፍ አለመፈለግ፣ መሠረታዊ በሚባሉት የመጠጥ ውኃ፣ የሞባይል ስልክና የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቶች የሚስተዋሉ የአገልግሎት መቆራረጦች ሊቀረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋዜጠኞች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ዕድል ከመስጠታቸው በፊት ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አገሪቱ ስላስመዘገበቻቸው ውጤቶች አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በእሳቸው ማብራሪያ መሠረት የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተጠናቀቀው ዓመትም በፈጣን ዕድገት ውስጥ አየተጓዘ ነው፡፡ ወደ መግለጫው ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ደርሶኛል ባሉት መረጃ መሠረትም የአገሪቱ የግብርና ዘርፍ ቀደም ሲል ከነበረው ዓመት የተሻለ ዕድገት ማስመዝገቡን፣ በተመሳሳይም የኢንዱስትሪ ዘርፉ ካለፈው ዓመት የተሻለ ዕድገት በተጠናቀቀው ዓመት ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውና ላለፉት ዓመታት ከሌሎቹ ዘርፎች የተሻለ ዕድገት ሲያስመዘግብ የነበረው የአገልግሎት ዘርፍ፣ በተጠናቀቀው ዓመት ያስመዘገበው ዕድገት ቀደም ሲል ከነበረው ቅናሽ ማሳየቱን፣ ነገር ግን የተመዘገበው ዕድገት በራሱ ፈጣን የሚባል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የምትገኝበት አካባቢ ለሽብር የተጋለጠ መሆኑን ከግምት በማስገባት መንግሥታቸው በአገሪቱ ደኅንነት ላይ ሲሠራ መቆየቱን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት በሚገባ የወከለ ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

ለመግቢያ እንዲረዳ ካቀረቡት አጠር ያለ ማብራሪያ በመቀጠል ጥሪ ለተደረገላቸው 30 የሚሆኑ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች መድረኩን ለጥያቄ የለቀቁ ቢሆንም፣ ከእርሳቸው ጥያቄ የመቀበልና ምላሽ የመስጠት ፍላጎት ጋር ያልተገናዘበ ፕሮግራም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ የተቀመጠ በመሆኑ፣ ጥያቄ መቀበል የቻሉት ከአምስት ጋዜጠኞች ብቻ ነው፡፡

ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል በኢሕአዴግ ውስጥ መከፋፈል መኖሩ እየተሰማ እንደሆነ በመጠቆም፣ በሊቀመንበርነት ‹‹የሚመሩት ፓርቲ ጤንነት እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ ይገኝበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ለዚህ ጥያቄ የመረጡት ምላሽ በጣም አጭር ነው፡፡ ‹‹በኢሕአዴግ ውስጥ መከፋፈል አለ የተባለው ምኞት ነው›› በሚል ብቻ የተወሰነ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ በገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ውስጥ መለስተኛ አለመግባባት መኖሩን፣ በተለይ ደግሞ ከኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የተሻለ ተሰሚነትና የበላይነት እንዳለው በሚነገርለት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ውስጥ አለመግባባት መኖሩ ይነገራል፡፡

በሕወሓት ውስጥ ያለው አለመግባባት የፓርቲው ደጋፊዎችን ጥያቄ ውስጥ የከተተ መሆኑንና በድርጅታቸው አካሄድ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ ማድረጉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ሕወሓት በተመሠረተበትና ሰፊ መሠረቱን በጣለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ጥያቄ እየተነሳ እንደሆነ ይናፈሳል፡፡

ግንቦት 7 የተባለው መቀመጫውን በውጭ ያደረገው ተቃዋሚ ድርጅት የገዢውን ፓርቲ አገዛዝ ለማብቃት የኃይል ትግልን እንደ ብቸኛ አማራጭ በመውሰድ በተለየ የትጥቅ ትግል ጥቃቱን ለመሰንዘር መሰናዳቱን በቅርቡ ስለማስነገሩና በአገር ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ ባካሄዱት ሰላማዊ ሠልፍ ለሚያነሱት ጥያቄ የመንግሥት ምላሽ ምንድን ነው የሚሉት ሌሎች የቀረቡ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽም ‹‹ግንቦት 7 ተናገረ ስለተባለው ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ ሕልም አይከለከልም፡፡ ሲነሱ ሕልም መሆኑን ያውቁታል፤›› ብለዋል፡፡

በአገር ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግ መብታቸው እንደሆነ በመግለጽ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቡት ጥያቄ ቀድሞውንም የታወቀና ከዚህ ቀደም መንግሥት ምላሽ የሰጠበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ፓርቲዎቹ በሚያቀርቡት ጥያቄ ላይ መንግሥት ያስተዋለው አዲስ ነገር ከዚህ ቀደም ቤት ውስጥ ሆነው ይጠይቁት የነበረውን አሁን በአደባባይ ነው እየጠየቁ ያሉት፡፡ ይህ መሆኑ ዲሞክራሲያዊ ስኬት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ፓርቲዎቹ እያነሱ የሚገኙት ከዚህ ቀደም የተነሳና መንግሥትም መልስ የሰጠበት በመሆኑ የምንሰጠው መልስ ምን እንደሆነ ነው ያልገባን፤›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርቲዎቹ ጥያቄ ምን እንደሆነና መንግሥት ከዚህ ቀደም ምን ብሎ ምላሽ እንደሰጠ ግን በዝርዝር የተናገሩት የለም፡፡ ቢሆንም ፓርቲዎቹ በዋናነት ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የፀረ ሽብር አዋጁ መሰረዝ እንደሚገባው፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱና መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በፓርቲዎቹ እየተነሱ ቢሆንም፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የውጭ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ካነሷቸው፣ መንግሥትን ከተቹባቸው፣ አሁንም የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሚወቅሱባቸው ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ላይ ለሚያቀርቡት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርት መንግሥት የተወሰኑ ምላሾችን መስጠቱን ከግምት በማስገባት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ለሚነሱት ጥያቄዎች ‹‹መንግሥት ቀደም ሲል ምላሽ የሰጠበት ነው›› ማለታቸው ከዚህ የመነጨ ይመስላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በዚህ ላይ ማብራሪያ ባይሰጡም፣ የፓርቲዎቹን ጥያቄዎች አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ቀጥለዋል፡፡ የቀጠለው ምላሻቸው ስላቅና ወደፊት ሊኖር ስለሚችለው የመንግሥታቸው ዕርምጃ የተካተተበት ነው፡፡

በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ወደ ዘጠና የሚጠጉ ፓርቲዎች እንዳሉ የተናገሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ‹‹ዘጠና ፓርቲዎች አሉ፣ ዘጠና እሑዶችን መጠበቅ ነው፤›› በማለት ፓርቲዎቹ እሑድ እሑድ ባደረጓቸው ሰላማዊ ሠልፎች በሚያቀርቡት ጥያቄ ተመሳሳይነት ላይ በስላቅ ተናግረዋል፡፡

‹‹መንግሥት ምን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ሊገባው አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄውን በተመለከተ መንግሥት አቋሙን ከዚህ ቀደም በግልጽ አሳውቋል፤›› የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ ፓርቲዎቹ ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሠልፍ ‹‹በየእሑዱ ጥበቃ ማቆምና ተመሳሳይ ጥያቄ ማድመጥ ያሰለቻል፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ተመሳሳይነት ያለው ጥያቄ ያነገበ ሰላማዊ ሠልፍ የሚቀጥል ከሆነ ‹‹ሠልፉ እንዲቆም ይደረጋል›› በማለት የመንግሥታቸውን የወደፊት ዕርምጃ አሳውቀዋል፡፡

ከተጠየቁዋቸው ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች መካከል በኢትዮጵያ የሃይማኖት አክራሪነትን የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ረዘም ያሉ ደቂቃዎችን በመውሰድና ጠንከር ያለ ድምፅ በመጠቀም የጉዳዩን አሳሳቢነት አንፀባርቀዋል፡፡

አክራሪነት በውጭ ኃይሎች የሚደገፍ አመለካከት መሆኑን በመግለጽ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንቅስቃሴው ሃይማኖትን ተገን ያደረገ በመሆኑ ከዋነኞቹ ጉዳዩ የገባቸው አራማጆች ይልቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃይማኖት ተከታይ ‹‹ፅድቅ የሠራ እየመሰለው ተሳስቶ የሚገባ ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹የአክራሪነት ትግል ለእኔ የፖለቲካ ትግል ነው፤›› በማለት በአገሪቱ የሚስተዋለውን ከሃይማኖት ተቋማት ተከታዮች ለሚነሳ ፖለቲካዊ ጥያቄ የመንግሥት ምላሽም ፖለቲካዊ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የአክራሪነት እንቅስቃሴ ዙሪያ መንግሥታቸው ቀይ መስመር እንዳስቀመጠ፣ ይህም የሌላውን እምነት መጋፋት እንደሆነ በመጠቆም ከዚህ መለስ ማንኛውንም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

‹‹ከቀይ መስመር በላይ መሄድ የሚፈልግ ይቆነጠጣል፤›› በማለት ጠንከር ያለ ዕርምጃ መንግሥታቸው እንደሚወስድ ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ባለማወቅ ከአክራሪዎች ጋር ተለጥፈው የሚሄዱ ራሳቸውን እንዲነጥሉ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፤›› በማለት መድረኩን ተጠቅመዋል፡፡

በኬንያ ናይሮቢ ከተማ የደረሰው የሽብር ጥቃት በኢትዮጵያ ላይ እንደደረሰ ይሰማናል በማለት ሐዘናቸውን በመግለጽ በሽብርተኝነት ላይ ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ከሽብርተኝነት ነፃ ነኝ ብሎ በአሁኑ ወቅት ማሰብ አይቻልም፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ሽብርተኝነት አሁን በማንኛውም አገር ውስጥ ያለ ፈተና መሆኑንና አደጋውንም በራስ ብቻ መታገል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ ሽብርተኝነት ሕዝብ ውስጥ የሚደበቅ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝብን ያሳተፈ ፀረ ሽብር ትግል ዋነኛ መሣሪያው እንደሆነ፣ የፀጥታና የደኅንነት ኃይል ደግሞ በተጨማሪነት እንደሚሳተፍ ተናግረዋል፡፡

 
Leave a comment

Posted by on October 5, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , , , , ,

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በግድ ዩኒቨርሲቲው እንዲለቁ ተደረገ


(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የሳይንስና ቴክኖሊጂ ተማሪዎች አስተዳደሩ COC (ፈተና) እንዲወስዱ በማስገደዱና ተማሪዎቹም ካለምንም ዝግጅት አንፈተንም፤ ጊዜ ሊሰጠን ይገባን በሚል ያነሱት አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ ተማሪዎቹ በግድ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።

ተማሪዎቹ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ፈተና ድንገት መውሰድ የለብንም ከተማሪዎቹ መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት ውጤት በማጣት ከትምህርት ገበታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ በሚል ስጋት ለማጥናት ጊዜ ይሰጠን ቢሉም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ምሳ እንደከለከልና ትናንት ጠዋትም ቁርስ ከከለከለ በኋላ አለመግባባቱ ተካሮ በመሄድ ማምሻውን ደግሞ ማደሪያም በመከልከሉ ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ካለምንም ህጋዊ ማስታወቂያ በአስተዳደሩ ሳቢያ በግድ ከዩኒቨርሲቲው ከወጡ በኋላ በአካባቢው ባሉ ቤተክርስቲያኖች፣ ሆቴሎችና በየሰው ቦታ እንደተጠጉ ተገልጿል።

posted by Endalkachew

 
Leave a comment

Posted by on October 4, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , , , , ,

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

 

 

 
Leave a comment

Posted by on October 1, 2013 in NEWS

 

Tags: , , , , , , , ,

ግንቦት ሰባት የኤርትራ ድጋፍ እንዳለው አስታወቀ ( VOA )

3333
“የወያኔን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዋነኛው አጀንዳዬ ነው” የሚለው ግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ በኤርትራ ምድር እንደሚንቀሣቀስና ከኤርትራ መንግሥትም እገዛ እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ ዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ትናንት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እያከናወንኩ ነው ስለሚላቸው እንቅስቃሴዎች መሪዎቹ ማብራሪያና ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

http://amharic.voanews.com/audio/Audio/328319.html

 
Leave a comment

Posted by on September 24, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , , ,

የአባይ ቡድን በሁለት ተከፈለ !!!

ccc
ህወሓት በአባይ ወልዱና ደብረፅዮን ቡድኖች በሁለት መከፈሉ ይታወቃል። ባለፈው የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የአባይና የደብረፅዮን ጠብ በጣም በመክረሩ የተነሳ ሽጉጥ መማዘዛቸው ተሰምቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝና በረከት ስምዖን ለማስታረቅ የሞከሩ ሲሆን ዉጤቱ አልታወቅም።

ይህ በንዲህ እንዳለ የአባይ ቡድንም ሰሞኑ በሁለት ተከፍሏል፤ የአባይ ወልዱና የበየነ መክሩ። ከህወሓት ስብሰባ በኋላ የስልጣን ሽግሽግ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም በየነ መክሩና ኪሮስ ቢተው ከስልጣናቸው ለመውረድ (ሓላፊነት ለመቀየር) ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከአባይ ወልዱ ጋር ከፍተኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል።

ኪሮስ ቢተው የግብርና ቢሮ ሓላፊና የኢንተርፕራይዞች የቦርድ ሰብሳቢ ነበር። አባይ ወደ ሌላ ቢሮ ሊቀይሮው አስቦ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። የኢንተርፕራይዞች (ብዙ በጀት የሚመደብበት) ስልጣን ግን ቀምቶ ለአለም ገብረዋህድ ሰጥቶታል። ግብርና ቢሮም ለወደ አዳል ታስቦ ነበር። ግን ጠብ ስለተነሳ አልተሳካም። በየነ መክሩም የንግድና ኢንዱስትሪ (የከተማ ልማት ጨምሮ) ስልጣን በእጁ ሲሆን አባይ ቢሮው ለሌላ ሊሰጠው ፈልጎ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ግን እስካሁን ውዝግብ ላይ ናቸው። በየነ መክሩ ወደ ሀገሩ (እስራኤል) የመሄድ ሓሳብ ይዟል። Read the rest of this entry »

 
Leave a comment

Posted by on September 22, 2013 in AMHARIC, NEWS

 

Tags: , , , ,

Police block Blue Party rally near Office

September 22, 2013

Blue Party Demo

Police blocked thousands of Blue Party demonstrators from rallying to the City’s biggest square, Meskel Square. They were blocked after they walked 100 meters from their Head office in Ginfele,near 4Kilo. The leaders of Blue Party have ordered demonstrators to return back to the Party’s Head Office and to peacefully continuethe demo there.  The demonstrators are voicing slogans like ” We Need Freedom, Police belongs to the people, we are one, Free Eskinder Nega, Free Reeyot Alemu and others”, sitting near their Head Office.

Blue Party’s earlier demo called on September 2, 2o13 had  been forcefully crushed by police. Police last week warned the Party that it could not only hold the rally in Meskel square but in Jan Meda.

 

Blue Party Demo Photo By Blue Party
 
Leave a comment

Posted by on September 22, 2013 in ENGLISH, NEWS

 

Tags: , , , ,