RSS

Category Archives: AMHARIC

Image

 
Leave a comment

Posted by on July 27, 2014 in AMHARIC, ARTICLE

 

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡

በኔ እምነት አይ ሲ ሲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት ትክክለኛውና ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስራውን በማከናወን ላይ ነው፡፡እስካሁን ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጥቂት ቢሆኑም ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርን አራዉተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡  የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ሲ ሲ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው ሊሰባሰቡ ነው፡፡
በኦክቶበር 11-12,  2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ  አንድነት ተዘዋዋሪ የ2013ቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው፡፡ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት ይሆናል፡፡ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው የ2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ ሲ ሲ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ ነው፡፡

ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ሲ ሲ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ሲ ሲ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ሲ ሲ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው  የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ ሲ ሲ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ  የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይይላሉ ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ  ለአይ ሲ ሲ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሲ ሲ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ ሲ ሲ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ ሲ ሲ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው?  እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲ ሲን ሲያቋቁሙ አይ ሲ ሲ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?

አይ ሲ ሲን በአፍሪካ አለሳልሶ የመግደል ጥበብ የሃይለማርያም ተንኳሽና የሚያስቆጣው ክሱ የሚያሳየው፤ አይ ሲ ሲን ከአፍሪካ በድል በማስወጣት እራሱን ‹‹ጭራቅ
ገዳዩ ጀግና›› ላመሰኘት የተነሳሳ መስላል፡፡ (የሱ ቀደምት የሥልጣን አባቱም ‹‹የአዲሱ ትውልድ አፍሪካዊ መሪ›› በሚል መጠርያ ለራሱ የፈረስ ስም ሰጥቶ፤ ታላቅ በመሆን በሽታ ተለክፎ ለማይለቅና ለማይድን እጀሰብ ተዳርጎ ነበር::) የነገሩ እውነታ መሰርት ግን በዚህ አካሄድ የሃይለማርያምና የጸረመስቀል ተዋጊዎቹ አካሄድ በኬንያዊያን ባለስልጣናት ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማስነሳት፤ በብዛት ከአይሲ ሲ አባልነት መውጣትን እንደማስፈራሪያና ማገቻ በማድረግ ወንድሞቹን ኬንያታንና ሩቶን ከአይ ሲ ሲ ማነቆ በማላቀቅ፤ ወደፊት በእነሱ ላይ ሊደርስ የማይችለውን አይቀሬውን ህጋዊ የክስ እርምጃ አስቀድሞ ለመዝጋት የሚያደርገው የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሕልም ሩጫ ነው፡፡ አፍሪካን በሚገባት ከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ላመስቀመጥ የሚጥረውን አይ ሲ ሲን ለማጥፋት ከንቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሃይለማርያምና መሰል ግፈኛ ገዢዎች ራሳቸውን ከግፍ ባህሪና ልምዳቸው በመመለስ እንደሰው በማሰብ ለሰብአዊ ፍጡራን ተገቢውን አገልግሎት ለማከናወን ቢተጉ ይበጃቸዋል፡፡

በኦክቶበር 11-12 2013 በአፈሪካ አንድነት ስለ አይ   ቀብር ስለሚደረገው ንግግር ቅድመ ትርኢት

የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች›› በኦክቶበር 11-12 2013 በአፍሪካ አንድነት በሚሰባሰቡበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት እብደት ቀረሽ ጸረ አይ ሲ ሲ  ዘመቻ በቂ ግንዛቤ አለን፡፡ የንግግራቸው መነሾና አካሄድየ አይ ሲ ሲን ወኔ ለመገድልና ተግባሩን ለማገድ አስቀድሞ ንድፉ በአምባሳደር ቋሚ ተወካይ ማቻሪያ ካማው፤ በኬንያ በተባበሩት መንግስታታ ቋሚ ሚሲዮን በኩል ለአምባሳደር ሜናንካዶ (የሴኪውሪቲ ካውንስል የሜይ ወር 2013 ሊቀመንበር) በተዘጋጀው ባለ 13 ገጽ ሚስጥራዊ ሰነድ ተዘርዝሯል፡፡

1. መላ የሌለውና ቅጥ ያጣ እርማት የተካሄደበት የካማው ሚስጥራዊ ሰነድ፤

ኬንያታን ሩቶ ከአይ ሲ ሲ ማነቆ ሊላቀቁ ይገባል ምክንያቱም እነሱን ለክስ ማቅረብ የኬንያን ልኡላዊነት ነጻነት የሚጥስ ነው፡፡ እንደ ካማው አባባል ‹‹የኬንያታና የሩቶ ክስ ራሱን ለሚያስተዳድረው መንግስታችን በውስጥ ጉዳያችንና በሃገራችን ኬንያና በልኡላዊነታችን ላይ የተቃጣ ውርደት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ የኬንያ ልኡላዊነት ከኬንያ ውስጥና ውጭ የተለያዩ ተዋንያንን በመጠቀም ለወቀሳ እየተዳረግን ነው፡፡እንዳለፈውና እንደተለመደው የሲቪሉን ማህበረሰብ በማነሳሳት የራሱን ፖሊሲ እንዲቃወም በመደረግ የሮምን ስምምነት ሰበብ በማድረግ አይሲሲን በአስፈጻሚነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡›› ነጻነት ለአፍሪካውያን ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች የመጀመርያው ስደተኛ ነው፡፡ አሁን የአፍሪካን ነጻነት ለማስከበር በማለት የሚንደፋደፉት አስመሳይ የአፍሪካ ጨቋኞች በኖቬምበር 2010 ምርጫ ወቅት ፈረንሳይ በቀጥታ በአይቮሪኮስት ግጭት ጣልቃ በገባችበት ወቅት፤ ገዳም እንደገባች አይጥ ተሸጉጠው ትንፍሽ ሳይሉ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን መልሳ ስተወር አንዲት ቃል አልተነፈሱም፡፡ የአፍሪካ አንድነትም ቢሆን በዝምታ ተቀምጦ ጠበይ ተመልካች በመሆን ከጎን ሆኖ ከመመልከት አላለፈም፡፡ በጃንዋሪ 2013 ፈረንሳይ የሰሜን ማሊን ከሽብርተኞች ወረራ ነጻ ለማውጣት ጣልቃ ሲገባ የአፍሪካ መሪዎች የፈረንሳይን ጦር ለማስወጣት የነጻነትንና የልእልና ማስከበርን ጉዳይ አላነሱም፡፡ አሁንም እንደገና የአፍሪካ አንድነት ከተመልካችነት አላለፈም፡፡

በወንጀል ፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት፤በጦር ወንጀለኛነት፤በዘር ማጥፋት ለሚሰነዘር ክስ ሉአላዊነት ሕጋዊ መከላከያ አለያም የፖለቲካ ውይይት ሁኖ አይቆምም፡፡ አሁን በአፍሪካ ፈላጭ ቆርጫ ገዢዎች የሚነሳው የሉአላዊነት ጥያቄ አይ ሲ ሲ የተጣለበትን አደራ ላማዘናገት ሆን ተብሎ የተነሳና ቀድሞ ከነበሩት የንጉሳዊ ገዢዎች በምድራዊ ዳኝነት እንጠየቅም ሥዩመ እግዚአብሔር ነን እንደሚሉት ለመሆን የታቀደ ዘዴ ነው፡፡ ሕገ ወጥ የሆነውን የአፍሪቃ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ሊዳኘው የሚገባውና የሚችለው ሌላው ሕገወጥ አፍሪካዊ ገዢ መሆን አለበት ነው የሚሉት፡፡

2.      ኬንያታና ሩቶ ከክስ ነጻ የመሆን መብት አላቸው ምክንያቱም በማርች 2013ቱ ምርጫ ‹‹ንጹህ›› ናቸው ስለተባሉ፤ካማው ኬንያታና ሩቶን በተመለከተ ሁለቱ ሰዎች ንጹሃን ብቻ ሳይሆኑ በክፍተኛው የመንግስት ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ሃለፊነትም አለባቸውና ክሱ ሊሰረዝላቸው ይገባል በማለት ይሞግታል፡፡ አይ ሲ ሲ የከፈተው የክስ
መዝገብ የሚዘጋበት ምክንያት ኬንታና ሩቶ የፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍረትና ጥሰት በፍትህ አደባባይ ቆሞ ስለሚመሰክርባቸውና ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል የንጹሃን ግፍና በደል በነሱ የስልጣን ወንበር መያዝ ተቻችሎ ነጻ ሊሆኑ ይገባል ነው፡፡  እነዚህ ሁለት ዋናና ምክትል ገዢዎች የኬንያውያን ሁሉ መተሳሰርያ በመሆናቸውና ሕዝቡም በፍቅር ስለመረጣቸው፤ 86 በመቶ ድምጹን ሰጥቶ መንበራቸው ላይ ስላስቀመጣቸው ክሱ ሊሰረዝላቸው ግድ ነው፡፡ ካሙ ክርክሩን በመቀጠል፤ የሮሙ
ስምምነት ኬንያታንና ሩቶ ሊያካትት አይገባም፤ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛውን የሃገሪቱን አመራር በዋናነትና በምክትልነት የያዙ በመሆናቸውና የኬንያ ሪፑብሊክ የመከላከያ አዘዦች በመሆናቸው፤ነው ይለናል፡፡ ካሙንን ግራ ያጋበው ነገር ኬንያታና ሩቶ ንፁህነታቸውን ለማረጋገጥ መመረጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በፍርድ ሸንጎ ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ ንጹህ ነውና፡፡ ስለዚህም በተጠረጠሩበት ወንጀል ኣይ ሲ ሲ የሚለው ችሎት ፊት ቀርበው ንጸህናቸውን በነጻ የፍትሕ ስርአት ያረጋግጡ ነው እንጂ ወንጀለኞች ናቸው ብሎ አልደመደመም፡፡ የሁለቱ ባለስልጣናት በአጥጋቢ ውጤት ከመመረጣቸው ጋር የተሰነዘረባቸው ተጠርጣሪነት አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ጥያቄው በ2007-08 በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ ተፈፀሙ በተባሉ ወንጀሎች ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ የሃገሪቱ መሪዎች መሆናቸው ከሕጉ ጋር የሚያገናኘው ሰበብ የለውም፡፡ የሮም ስምምነት አንቀጽ 27 ማንኛውም ተጠርጣሪ አይሲሲ ችሎት ቀርቦ ንጽህናውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ይላል፡፡ ስምምነቱ ማንንም በእኩል ደረጃ ይመለከታል፡፡ ማንንም ከማንም በስልጣን ደረጃ አያመዛዝንም ለአይ ሲ ሲ ምንኛውም ተጠርጣሪ እኩል ነው፡፡ ተመራጭ ፕሬዝዳንትም ይሁን የፓርላማ አባል የመግስት ባለስልጣንም ሆነ ተራ ዜጋ ለአይ ሲ ሲ ችሎትና መመርያ ሁሉም እኩል ናቸው፡፡

በኬንያታና በሩቶ ላይ የተመሰረተው ስንኩል ክስ (የተባበሩት መንግሥታት ሴኩሪቲ ካውንስልና በኬንያም መንግሥት ወንጀል መስራታቸው ሳይተላለፍለት ነው) በአግባቡ ምርመራና ማጣራት ሳይካሄድበት ነው ይላሉ፡፡ የአይ ሲ ሲ ክስ ተቀባይነት የሌለው ምስክሮቹንም አስጠንተው ያቀረቧቸው ናቸው፡፡ ተጠቂ ነን ብለው የቀረቡትም ሃሰተኞች አለያም ተመርጠው የተሰየሙ ናችው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ደካማና የማያሳምን ነው፡ በማለት ካሙ ይከራከርላቸዋል፡፡ ምስክሮች  በመደለያ የተገዙ ያንንም ነው አይደለም ብሎ የሚወስነው የአይ ሲ ሲ ችሎት ነው፡፡ ምናልባትም ምስክሮቹ ተአማኒነት የሌላቸው በጥቅማ ጥቅም የተገዙ ናቸው የሚባልም ከሆነ የካሙስ መንግስት ማስረጃውን በማቅረብ ሊቃወም ይችላል፡፡

4.      የአቃቤ ሕግ ቢሮ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ በኬንያታና በሩቶ ላይ የክስ ምስረታውን ተከሳሾቹን በሚጎዳ መልኩ እያካሄድ ነው ለፍትሕ በእኩል መልኩ የተከናወነ አይደለም በማለት ተጠርጣሪዎቹን ተከሳሾች ፍትሕ በአግባቡ ነጻ ናቸው አይደሉም ከማለቱ ይልቅ አይ ሲ ሲንና የአቃቤሕግ ቢሮን በሃሰት በመወንጀልና ፍትሕ ገደል ይግባ ለኛ በሚመቸን መልኩ የማይሰራም አይ ሲ ሲ ፍርስርሱ ይውጣ የሚል ነው የካማው ቅጥ ያጣ ሙግት፡፡ ፍትሕ ለመዛባቱ የካማው መንግስት ማስረጃ ካለውና በፊትም ሆነ አሁን ኬንያታንና ሩቶን ፍትሕ ይነፍጋቸዋል ብሎ ካሰበ ወደ ፍርዱ መድረክ በማቅረብ ሕዝብ እንዲያውቀው ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ በተቃራኒው ካማውና የአፍሪካ መሪዎች ሊያደርጉና ለማድረግም በመጣር ላይ ያሉት አንዳችም እውነትነት የሌለው የክስ ዳውላ በመዘርገፍና እርፍት የለሽ የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ዓለምን ሊያሳምኑ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እውነት ካላቸው እነካማው አለን የሚሉትን የፍትህ ግድፈት አደባባይ ያውጡት፡፡

5. አይ ሲ ሲና የአቃቤው ሕግ ቢሮ ማንም የማይቆጣጠረውና ከሕግ ውጪ ለማንም ተጠያቂ ያልሆነ ባለሥልጣን ነው ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ ዓለም አቀፋዊ ተቋም የሃገራትንና የዜጎቿን ሕጋዊ ግዴታ ለመመልከትና ለመወሰን ወንጀልም ሲያገኝባቸው በአግባቡና በስርአት ቅጣት ለመጣል ተመስርቷል፡፡ አይ ሲ ሲ ብቃቱን በተመለከተ በማንኛውም መልኩ ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ምን እንደሚያስፈልገው ሲረዳ የመከራከሪያው የመጨረሻ ቃላት አይ ሲ ሲ ሲወስን በማንኛውም መንግስት ቁጥጥር ስር አለያም ትእዛዝ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕግጋት በሚመሩበት ስርአት ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ካሙ የሚያውቀውና የሚለውም ሆነ አይ ሲ ሲ ያድርግ የሚለው አለቆቹ በሚወነጀሉበት ጥፋታቸው ሁሉ አስቀድሞ እነሱ የሚያዙት ችሎታቸው ጉዳዩን ይመርምር ነው፡፡ የሚያውቀውና የሚከተለው አሁን ምርመር ይደረግባቸው የተባሉት አለቆቹ ሲያስሩ ሲገድሉ ሲያሰቃዩ ፍርድ አልነካቸውምና አሁን እንዳይነካቸው ይደረግ ነው፡፡ ካሙ ችግሩና በሽታው አለቆቹ የሚመሩበት ያልተጻፈ ሕግና ያልተሰጣቸውን ስልጣን መጠቀም ስለሆነ በዚያው መሰረት ይዳኙ ነው፡፡ አይ ሲ ሲ የሚታዘዘውም ሆነ የሚመራው በዓለም አቀፉ የፍትሕ ስርአት ነውና ማንንም አይጠላም ማንንም ከማንም አስበልጦ አያፈቅርም፡፡ ካሙ ለምን አንድ አቃቤ ሕግ ብቻውን ያጣራው ጉዳይ ተቀባይነት ያገኛል ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ደግሞ አቃቤ ሕግ ግድፈት አለበት የሚል ማንኛውም ተጠርጣሪ አለያም ዜጋ መስረጃውን አቅርቦ ሊሞግተው ይችላል ነው፡፡

የአፍሪካን ዲክታተሮችና ጭፍሮቻቸው ስለ ‹‹ቁጥጥር አልባ ሥልጣን›› ሲያወሩ ማዳመጥ የአዞ እንባ እንዲሉ አይነት ነው፡፡ የኬንያን ባለስልጣነት መጠን የለሽ የስልጣን ክልል በመጠኑም ቢሆን ለመቆጣጠር ያስቻለው በ2010 የወጣው ሕገመንግስት ነው፡፡ በኬንያ ስርአት አልበኝነትን ሕገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የወጣው አዲሱ ሕገመንግስት  ነው መሰረት የጣለው፡፡ ማንም ሊረዳው የሚገባው አዲሱ የኬንያ ሕገመንግስት በ2007 በተከሰተው የምርጫ ውዝግብ ሳቢያ በተካሄደው ውይይት ላይ ተመስርቶ መረቀቁና መጽደቁ ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ በዚያው ሕገመንስት ደንብና ስርአት  ውስጥ በተካተተው መመርያ መሰረት ነው ለፍርድም ሊቀርቡ ማዘዣ የወጣባቸው፡፡

በአፍሪካ የሕግ የበላይነት እነ ካማው መሰረተ ቢስ የሆኑ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት ሕዝብንና መንግስታትን በማታለልና መንገድ በማሳት አለቆቻቸውን ነጣ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እነ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአይ ሲ ሲ አካሄድ ማንም ግፈኛና ወንጀለኛ ከነጉድፉ ተሸሽጎ እነዳይኖርና ግፍና በደሉን በማር ቀብቶ ለማስመሰያነት እንዳዋለ እንዳይኖር  የማድረግ ስልጣኑ ማነህ ባለሳምንት ይለናል በማለት አስቀድመው ለራሳቸው የሚጠቅም ከለላ ለመፍጠር ነው ጥረታቸው፡፡ የዓለም ሕግ ተፋለሰ ሲሉ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ የኡኡታ አሰሚዎች የፈጸሙትን የሕግ መፋለስ በመዘንጋት ሳይሆን አውቀው ትክክለኛ መስለው ለመታየት እንጂ በአይ ሲ ሲ አካሄድ የተፋለሰ አንዳችም ሕግ የለም፡፡ አለ ከተባለ ደግሞ ከነማስረጃው ማቅረብ እንጂ ከንቱ የጋጋኖ ጨኸት የትም አያደርስም፡፡ የአፍሪካ አንድነት ደንብም ቢሆን በአፍሪካ ውስጥ ሰብአዊ መብት ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባው ይደንግጋል፡፡ ስለመልካም አስተዳደርም በደንቡ ላይ አስፈሯል፡፡ ማንም ከወንጀል ነጻ ሊሆን እንደማይችል ደንቡ ያናገራል፡፡

በኦክቶበር 13 ለቁጥር የሚጣክቱት መሪዎች ከሮሙ ስምምነት ለመውጣት ማሴር ማለት ሕግ አልበኝነትና የራሳቸው የአፍሪካ አንድነት የሚተዳደርበትን ደንብ መጣስ መሆኑን መዘንጋት ነው፡፡ ተጠያቂነትን ያወጁ ሃገራት ተጠየቁ ሲባሉ ሕጉን ያወጣነው ሕዝብን ለመቅጣት እንጂ እኛ ልንጠየቅበት አይደለም ማለት ምን የሚሉት፡፡ በጣም ቀላል የሆነና የማይቀር ምርጫ አለን፡፡እነዚህን በአፍሪካ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ሆነው ግፍን በመፈጸምና ሃላፊነትን አላግባብ በሚጠቀሙ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከሮም ውልና ስምምነት የመውጣት አድማቸው ላይ አቋም በመያዝ መመጎት ቢያንስ  የነዚህን እኩዮች አድማ የሚቃወሙትን ተቆርቋሪ ወገኖች ማገዝ ነው፡፡ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት መቆምና መወገን ማለት አፍሪካ ውስጥ በመግዛትና ግፍ በመፈጸም ያሉትና ባለስልጣናት መሞገት ነውና አብረን ሆነን ከአፍሪካ ጫንቃ ላይ እንዚህን ጋሬጣዎች እንንቀስ! አይ ሲ ሲን የመደገፊያው ወቅት አሁን ነው::

 
Leave a comment

Posted by on October 16, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , , , , ,

በደብረ ማርቆስ ዩነቨርስቲ ተማሪዎችና በመንግስት መካከል ረብሻ ተነስቷል

(ዘ-ሐበሻ)  ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና በመንግስት መካከል ውጥረት ነግሷል፡፡ የችግሩ ዋነኛ መንስኤም በግቢው በሚቀርብ ምግብ ዙሪያ እና መንግስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ኃይማኖታዊ ስርዓትን
የተላበሰ አለባበስ መልበስ የተከለከለ ነው በሚል በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተካታዮችና የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ድርጊቱን በመቃወማቸው ረብሻ ተቀስቅሷል፡፡ በዚህም በተፈጠረ አለመግባባት የፌደራል ፖሊስ ተማሪዎችን እየደበደበ ከግቢ ያስወጣ ሲሆን፤በዚህም የቆሰሉ ተማሪዎች እንዳሉ እና በአሁን ሰዓትም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተለይ ትናንት ሰኞ ማታ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በርካታ ተማሪዎች በፈደራል ፖሊስ እየታደኑ እየታሰሩ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን በከተማው ያሉ ወላጆችም በጉዳዩ እጅግ በመቆጣታቸው በዚህ ምሽትም በርካታ ወላጆችም በተማሪዎቹ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ በመቃወም ከቤታቸው ውጭ ከፌደራል ፖሊስና ከአማራ ክልል ፖሊስና አስተዳደር ጋር መፋጠጣቸውም ተነግሯል፡፡ በተፈጠረው ችግርም እስካሁን ምን ያህል ተማሪ እንደተጎዳ በቁጥርና መጠን ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የዩኒቨርስቲው አስተዳደርንና የአማራ ክልል አስተዳደርና ፖሊስን  ለማናገር ብንሞክርም ስልካቸው ዝግ ነው፡፡ የነበረው አለመግባባትም ይህ እስከተዘገበበት ድረስ በግቢው በደንብ አለመረጋጋት እንዳለም ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

 
Leave a comment

Posted by on October 15, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , ,

በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተለቀቅን!!! ዜጎችን በፖለቲካ አቋማቸዉ ማሰርና ማዋከብ ይቁም!

ጓዶች ተመልሰና . . . ጉድ አይተን . . . ያዉ የኛ ጉዳይ ሲለመድ እስር እና ዱላ እንደ ተራ ነገር እያየነዉ ምንም አልመሰለኝም ነበር . . . ያሁኑ ግን እኛን እያዋከቡና እየሰደቡ ወደ ዉስጥ ሲያስገቡን ከዉጪ ሆነዉ እኛም ከነሱ ጋር ነን እኛንም ዉሰዱን ባሉ ጓደኞቻችን ላይ የደረሰባቸዉ ድብደባና ስድብ አፀያፊ ብቻ ሳይሆን ምን ያህል ፖሊስ ገለልተኛ እንዳልሆነ በይበልጥ ግልፅ አድርጎታል . . . አንዳንዶቹን በጃቸዉ የነበረ መፅሃፍና መፅሄት በመንጠቅ “አሁን እናንተ ስለፖለቲካ ምን ታዉቃላችሁ” እስከማለት የደረሰ የአምባገነን ወገንተኝነት አንፀባርቀዋል፡፡ ባዛም አካባቢ እንዳይቆሙ አመራሮችን ሳይቀር በቆመጥ እየመቱ አብረዋቸዋል፡፡ ዉስጥ የገባነዉም ብንሆን ሞራላችንን ለመንካትና ለማሸማቀቅ ያልተባለ ነገር የለም . . . አንዱ “አንዴት ብትደፍሩ ነዉ በኛ ክልል(ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ) የምታልፉ” ሲል . . . አንዷደሞ (ለስሙ 3 ኮከብ በትከሻዋ ተደርድሯል) ቀበል አድርጋ ለምን “የማይገፋ ትገፋላችሁ አርፋችሁ ቁጭ ብትሉ ይሻላችኋል” ብትለንስ!!! በነገራችን ላይ ነሀሴ ላይ ታስረን ስንደበደብ “ለነዚህ ደርግ ነበር የሚሻላቸዉ” ብላ ከኢህአፓ ጋር ያመሳሰለችን ‘ሰዉ’ ናት (ጌታ ልብ ይስጣት). . . ብቻ ምን አለፋችሁ ብዙዉን እዚህ መነሳት የሌለበት ጉድ ትተን ለመብት መከራከር በተረጋጋ ሁኔታ ስለሁኔታዉ መነጋገር ፤ ቃል አልሰጥም ማለት ፤ ለምን ማለት እንደ ወንጀለኛ ያስቆጥር ነበር፡፡ ገና ሲይዙን ጀምሮ ሰማያዊዎች መሆናችንን ሲያዉቁ አንደሆነ ነገር ነበር ያደረጋቸዉ አጃኢብ ነዉ ሰዉ የገደለ እንኳን እንዲህ አይንገላታም በስእብናዉ ላይ መንቋሸሽ አይደርስበትም!!!

የሆነ ሆኖ በዚህ መልኩ ታስረን እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት መኪና የለም በሚል ብርድ ላይ አቆይተዉን ኋላም ወደ ወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ ተወስድን እዛ ነበር በይበልጥ አሳዛኙንና ሊታረም ይገባዋል የምንለዉን አሳዛኝ ሁነት የታዘብነዉ(ስለ እስረኛ አያያዝ በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ) . . . እናም በዚህ ማቆያ እስር ቤት ቅዳሜን እና እሁድን አሳለፍን፡፡ ሰኞ ሲደርስ እንደለመዱት ሊፈቱን ምንም እንዳልተፈጠረ ሊለቁን አማራቸዉና እንደለመዱት ዉጡ ተባልን ይህ ጨዋታ ግን በኔም ሆነ በጓደኞቼ አልታመነበትም ነበርና ለፍርድ ካልቀረብን አንወጣም አንፈታም አልን . . . በሰዓቱ በቦታዉ አንዳንድ የደህንነት አባላት የነበሩ ሲሆን ሁኔታዉን ለአለቆቻቸዉ ደዉለዉ ሲያስታዉቁም ታዝበናል . . . በአንዳንድ የፖሊስ አባላትም በሁኔታዉ የመገረምና የመናደድ ነገር ታይተባቸዋል፡፡ ግን በኛ እምነት ማኛዉም አካል ሲታሰር በወንጀለኝነት ተጠርጥሮ ወይም እጅ ከፍንጅ ተይዞ ሲሆን ከዛም ነፃ መልቀቁም ሆነ ወንጀለኛ ማለቱ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ነዉ ነገር ግን በተደጋጋሚ ጊዜ የኢህአዲግን የአፈና ስራ በሚፈፅሙለት ፖሊሶች ታስረን ተደብድበን ምንም እንዳልተፈጠረ ሂዱ ከዚህ ጥፉ ከማለትም አልፈዉ አላሰርንም እስከማለት ይዋሹ ነበር ያ ግን መስዋዓትነት ተከፍሎበትም ቢሆን መቅረት ያለበት የመንግስት ሸፍጥ ነዉ . . . ወደ ነገሩ ስንመለስ ከወረዳ 9 ወደ ጃንሜዳ መልሰዉን በቀበሌ መታወቂያ ዋስ ጠርተን እንድንወጣ ማስፈራራት በሚመስል መልኩ ቢነግሩንም ሳንስማማ ቀረን በኋላም ሃሳባችን እንደማይቀየር ሲያዉቁና አንደተረዳነዉም ከአለቆቻቸዉ በደረሰባቸዉ ጫና በቀላል ወንጀል መለትም ሁከት ለመፍጠር በሚል ክስ በፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡብን አሳወቁን . . . ጉዞም ወደ ችሎት መድሃኒዓለም የ8 ሰዓት ምድብ ሆነ እዛም እንደደረስን ዳኛዋ ክሱን ላለመቀበል ብትፈልግም በሆነ መንገድ እድንገባ ተፈቀደ በሂደቱም የፖሊስ አቃቢ ህግ ገና ክሱን እያጣራሁ ነዉ ስላለ እንዲሁም በፍርድ ቤቱ የክሱ ሀተታ አሳማኝ ስላልነበረ ያለአግባብ እንደታሰርንና በሰንበት እንደተንገላታን አሳስባ ባስቸኳይ በመታወቂያችን ዋስ እንድንወጣ በትናንትናዉ ዕለት ወሰነችልን!!!

ዋናዉ ነገር ይህ የትግሉ በጣም ትንሹ ነገር ሲሆን ገና ብዙ እንደሚጠብቀን እያሰብን እንደእኛም ሰዉ ሆነ እንደ ሰማያዊ ከተነሳንለት ዓላማ አንዱ ከፍርሃት ተላቀን ማንኛዉም ሰዉ ከህግ በላይ እዳልሆነ እንዲረጋገጥ ከትንሹ ይህን ከመሳሰሉ አጋጣሚዎች በመጀመር ወደ ከፍተኛ ጉዳዮች መድረስ መቻል ነዉ . . . ይህም አካሄድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዉጤታማ እያደረገን ይገኛል፡፡

ማናችንም ብንሆን ነፃነታችንም ሆነ ዲሞክሪያሳዊ መብቶቻችን በሆነ አካል በቸሮታ የሚለገሱን ሳይሆን በራሳችን ትግል ለራሳችን ምናጎናፅፋቸዉ ሰብዓዊ እኛነታችን ናቸዉ ስለዚህም ከትንሹ ጀምረን መታገል ለመብታችን መቆም ያለህግ የሚደረጉ ክንዉኖችን እምቢ አልተባበርም ማለትና እነዚህንም ማጋለጥ ግዴታ አለብን! በመጨረሻም በመታሰራችን ለተጨነቃችሁና በሁሉም መልኩ ድጋፍ ላደረጋችሁልን ሁላ ዝቅ ብለን አመሰገንን!!!

Amha Teresa

 
Leave a comment

Posted by on October 15, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , , ,

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡
የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ህገ መንግስቱ በግልጽ እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሊጠይቋቸው በሚፈልጓቸው ሰዎች መጎብኘት እንደሚገባቸው ቢደነግግም የቃሊቲው መንግስት ግን ህገ መንግስታዊውን ድንጋጌ በመጣስ በማን አለብኝነት የእስክንድር ጠያቂዎችን በዝቅተኛ ቁጥር ገድቧል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ምንጮች እስረኞች ጥፋት ሲፈጽሙ እንዲህ አይነት ህግ ለተወሰነ ግዜ እንደሚወጣባቸው በማስታወስ በእነ እስክንድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ ግን ‹‹ጥፋት መፈጸማቸው ሳይነገራቸው ፣ፈጸሙት ለተባለው ጥፋትም ቀርበው መከራከሪያ ሳያቀርቡ መሆኑ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ያደርገዋል››ብለዋል፡፡
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ሰዎች ውጪ እንደማትጎበኝ እርሷን ለመጠየቅ የሚፈቀድላቸው ሰዎችም ለአስር ደቂቃ ብቻ እንደሚያገኟት ከዚህ ቀደም መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

 
Leave a comment

Posted by on October 15, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , , ,

Part 2 የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካ የሚገኙትን አቶ ስብሃት ነጋን አፋጠጣቸው ድምፃችን

 
Leave a comment

Posted by on October 12, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , ,

ከ15 ሺ በላይ የኢህአዴግ አባላት መልቀቂያ አስገቡ

ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው የአባላት ግምገማ ወቅት ከ15 ሺ በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይፋ ተደርጓል።

ስራቸውን ከሚለቁበት ምክንያቶች መካከል በድርጅቱ አመኔታ ማጣት ፣ ተገቢውን አገልግሎት ክፍያ አለማግኘት፣ ለድርጅቱ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍተኛ መሆን እና የድርጅቱ አባላት ሹመት በወገን መሆኑ የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ከፍተኛ የአባላት መልቀቂአ ቁጥር ከተመዘገበባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ በ9 ሺ 4 መቶ 56 አንደኛ ሲሆን ፣ አማራ፣ ደቡብ ክልል እና ትግራይ በተከታታይ ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል። በትግራይ በ2005 ዓ/ም 1 ሺ 1 መቶ 13 ሰዎች የህወሀት አባላት መልቀቂያ አስገብተዋል።

ኢህአዴግ 5 ሚሊዮን አባላት እንዳሉት ቢነገርም ፣ በንቃት የሚሳተፉት 2 ሚሊዮነቹ ብቻ ናቸው ተንብሎአል። ከእነዚህ መካከል 20 ሺ የሚሆኑት በስም ብቻ አባላት ተብለው ቢመዘገቡም፣ በአካል የሌሉ መሆናቸውም ተገልጿል።

በስብሰባው አብዛኞቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለደሞዝና ለስራ ሲሉ አባል እንደሚሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በአለፉት አመታት ድርጅቱን ከተቀላቀሉት ተማሪዎች መካከል ስራ አገኙት ሩብ አይሆንም ተብሎአል።

በክልል ዋና ዋና ከተሞች በአዋሳ፣ ባህርዳር፣ እና መቀሌ ውጤት ያላቸው ተመራቂዎች ስራ ሳይዙ፣ ውጤት የሌላቸው የድርጅቱ ነባር አባላት በተቃራኒው ስራ መቀጠራቸው በአባላቱ ላይ ቅርታ እንዲፈጠር አድርጎአል ተብሏልም ።

ዛሬ ስራ ማግኘት የህልም እንጀራ ነው ያሉት አባሎች፣ ዲግሪ ይዘው ስራ ለማግኘት ከሶስት እስከ 4 አመታት የሚጠብቁ ተመራቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ኢህአዴግ መልቀቂያ ያቀረቡ አባላቱን ጥገኞች ሲል ሰይሞአቸዋል። የድርጅቱ አባላት ለኢሳት እንደገለጹት አብዛኞቹ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ኢሳት በሚቀጥለው ሳምንት <<የድርጅት አባላት እንዲያውቁት>> በሚል የብአዴን የአመራር አባላት ሙስናን በተመለከተ የላኩትን ደብዳቤ ይፋ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ይወዳል።

በተመሳሳይ ዜናም አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ትናንት ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት ተበትኗል።

መንግስት ንጹሀንን ያለምንም መረጋገጫ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው”ያሉት የስብሰባው ተሳታፊዎች፤”በመንግስት እየተባለ ያለውን ነገር+ እንኳን የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ፤ሳይማሩ እያስተማሩ ያሉት እናት አባቶቻችንም አይቀበሉትም “ብለዋል።

ተማሪዎችና መምህራን በማከልም፦”የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል” በማለት የመንግስት ባለስልጣናትን ሞግተዋቸዋል።

“ጽንፈኛ” የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት አንድ ክርስቲያን የሆኑ የስብሰባው ታዳሚ፤ “መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች በክርስቲያኑ ላይ ጦርነት ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ፤ህዝበ ክርስቲያኑ አይቀበለውም”ብለዋል።

ግለሰቡ አስተያየታቸውን ሲያጠቃልሉም፦ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘና ተዓማኒት የሌለዉ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ቢ.ቢ.ኤን ዘገባ፤በስብሰባው ላይ በዩንቨርሲቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለ የቀረበው ሃሳብ በሁሉም ተሳታፊዎች ከፍ ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል።

“ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መከበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም፤”ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ሰዎችአለባበሳቸዉን ከቀየሩ አመለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ ስህተት ስለሆነ “ሀይማኖታዊ አለባበስ ከዩኒቨርሲቲ በር መልስ”የሚለው ሃሳብና እቅድ ተቀባይነት የለውም”ብለዋል።

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሐረማያ ዩኒቨርስቲ” አክራሪነትንና አሸባሪነትን” አስመልክቶ ባዘጋጀዉ በዚህ ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

ይሁንና በርካታ ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ ፊት ለፊት በንግግር ከመቃወማቸውም በላይ ስብሰባዉን ረግጦ ወጥተዋል።

 
Leave a comment

Posted by on October 12, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , ,

የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!

የኢህአዲግ አፈና በሰማያዊ አመራሮች እና አባላት ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዉስጥ ለሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተከራይቶ የነበረዉን ቤት ከዛሬ ጥቅምት 1 2006 ጀምሮ ለመጠቀም በሄዱበት ጊዜ የክፍለ ከተማዉ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን አማረ ፤ የወረዳዉ አስተዳደር ሃላፊዎች ፤- የወረዳ 3 ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ቤካ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አማረ አቡጤ ፤ መነን አካባቢ ፖሊሶች ፤ ፌደራል ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ የደህንነት አካላት በጋራ በመሆን በማይመለከታቸዉ ጉዳይ የፓርቲዉን ከፍተኛ አመራሮች
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት(ሊቀ መንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (ምክትል ሊቀመንበር)
3. አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ (የህግ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ እንዳሻዉ እምሻዉ (የጽህፈት ቤት ሃላፊ)
5. አቶ በቃሉ አዳነ (ምክር ቤት አባል )
6. አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
7. አቶ ብርሃኑ ተክለ-ያሬድ (አባል)
ወደ መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንገልፃለን፡፡አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረዉን ቤት ‘ለወሔነት’ ባርና ሬስቶራንት ለፔንሲዮን አገልግሎት እንዲሚጠቀምበት ቢሆንም የፔንሲዮኑ ባለቤት የሆኑት አቶ በላቸዉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ 3 አስተዳደር በግዴታ እንዲከራዩ የእያስገደዷቸዉ ሲሆን አቶ በላቸዉና የቤቱ ባለቤቶች እኛ ተገደን ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቤቱን ለፓርቲ ጽ/ቤት እንዳይከራይ እየተከራከሩ ያሉት በአቶ ያለዉ እዉነቱ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ የሚመሩ የመስተዳድሩ አካላት መሆናቸዉ በይበልጥ ለፓርቲዉ ጽ/ቤትነት ለመጠቀም እንዳንችል መንግስት እጁ እንዳለበት መገንዘብ ተችሏል፡፡ 
በአሁኑ ወቅት በመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የፓርቲ አመራሮች ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸዉን አሁን የደረሰን መረጃ ይገልፃል፡፡

 

 
Leave a comment

Posted by on October 12, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , , ,

ህወሃቶች ነፃነት ያለውን ህዝብም ለመምራት ብቃት የላቸውም።(እንዳልካቸው ጉሉማ ከኖርዌይ)

 

የነፃነትን ዋጋ የተረዳና ነፃ የሆነ ማህበረሰብን የሚመራ ሰው ምርኩዙ የማይሰበር የታመነ ነው።የህዝቡን ነፃነት ገፍፎ አገርን እመራለሁ የሚል ግን ምርኩዙ ሸንበቆ፤ የተሰበረ ዕለትም ተመልሶ የሚወጋው ነው። ህወሃት እንዲያ ነው። የዜጎችን ነፃነት ገፎ በጉልበቴ እገዛችኋለሁ እያለ ነው። ምርኩዙ የታጠቀው መሣሪያ እንጂ ህዝቡ አይደለም። ይህ ታጠቅን ብለው የሚመኩበት መሣሪያ የሸንበቆ ምርኩዝ ነው። በዚህ መሣሪያ አስገድጄ ህዝብን እገዛለሁ የሚል ቡድን ሲሰበር ተመልሶ የሚዋጋን የሸንበቆ ምርኩዝ ተመርኩዞ የቆመ አንካሳ ሰውን ይመስላል።የህወሃት አቋም እንዲያ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ልጅ ከፈጣሪ የተሰጠውን ታላቅ ስጦታ አስነጥቆ መኖርን እሺ ካለ ያተርፍበት ዘንድ የተሰጠውን መክሊት  መሬት ምሶ የቀበራትን ያንን  ሰነፍ ሰው ሆነ ማለት ነው። ነፃነታችን ሠርተን ፍሬ አፍርተን እንኖርባት ዘንድ የተሰጠችን ዋጋ ያላት መክሊት ነች። ነፃነት ፍሬዋ በገንዝብ አይተመንም እንጂ ብዙ ሚሊዮን ዋጋ ባወጣች ነበር። ነፃነታችንን ሰጥቶ የፈጠረን እግዚአብሄር ስንት ያወጣል እንደማይባል ሁሉ ነፃነታችንም በገንዘብ የምትገመት አይደለችም። ህወሃት ሊፈጠራት በሚሞክራት ኢትዮጵያ ግን ነፃነታቸውን ለገንዘብ ሲሉ አሳልፈው የሚሰጡ ለራሳቸው ክብር የሌላቸው ግለሰቦች እንደ አሸን ፈልተዋል። ነፃነት ለድርደር የሚቀርብ ነገር አልነበረም። ነፃነታችንን ሰጥተን የምንቀበለው ሌላ ምንም ነገርም አልነበረም። ህወሃት ግን የዜጎችን ነፃነት በሚበላና በሚጠጣ ከንቱ ነገር ገዝቶ አገሪቷን ለመምራት ይሞክራል። ይሄ ዘረኛ ድርጅት ምኞቱ ዜጎች ነፃነታቸውን ተነጥቀው ዝም ብለው  ከሰው ተራ ጎድለው እንዲኖሩ ነው። ይሄ ደግሞ ለራሳቸው ክብር በሚሰጡ ዜጎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው አይደለም።ለራሱ ክብር የሚሰጥ ሰው ነፃነቱን ተነጥቆ ዝም አይልም እንዲያውም “ነፃነቴን ወይም ሞቴን” ብሎ ይነሳል።

ዛሬ በአገራችን ደምና አጥንታቸውን ቆጥረው የተደራጁ ራሳችውን “የትግሬ ነፃ አውጪ” ብለው የሚጠሩ ቡድኖች የእግዜር ስጦታ የሆነችውን ነፃነታችንን ነጥቀው ከሰው ተራ አጉድለው ሊገዙን ተማምለዋል። ለዚህም መሃላቻው ለሚበላ እና ለሚጠጣ ከንቱ ነገር ብለው መኪልታቸውን የሸጡላቸውን አልባሌ ሰዎች ከጎናቸው አሰልፈዋል። እነዚህ ቡድኖች የነፃነትን ዋጋ ሳያዋቋት ነፃ አወጣናችሁ ይሉናል። እነርሱ ሁሉን አድራጊ ሁሉን ፈጣሪ፤ እነርሱ ሰጪና ከልካይ መሆን መቻላቸውን ነፃነት ብለው ይጠሩታል። ይሄም ምንኛ ከዚህ ዘመን ጋር አብረው መሄድ የማይችሉ የጭለማ ንጉሶች እንደሆኑ አመላካች ነው። እነዚህ የጨለማው ነገስታት በምንም መሠፍረት አገራችንን ለመምራት የሚመጥኑ አይደሉም። አገራችንና ዜጎቿ ከህወሃት በላይ በጣም ከፍ ያሉ ናቸው።ህወቶች ነፃነትን አያውቁም። ነፃነት ያለውን ህዝብም ለመምራት ብቃት የላቸውም። ምርኩዛቸው ህዝብ ሳይሆ የያዙት የመሣሪያ ብዛት፤ እምነታቸው እውነት ሳይሆን ውሸት ነው። በመሣሪያ ብዛት እና በውሸት ላይ ቆሞ እሰከ መጨረሻው መዝለቅ እንደማይቻል በዙሪያቸው ከሚከሰተው ሁኔታ አንኳ መማር የማይችሉ ልበ ደንዛዞች ናቸው። ተመርኩዘው የቆሙት የሸንበቆ ምርኩዝ ነገ ሲሰበር ተመልሶ እንደሚወጋቸው ለመረዳት ብርቱ የሆነ የአስተሳሰብ ችግር አለባቸው። የነገውንም አርቀው ለማየት አቅም ያላቸው አይደሉም። እነዚህን ቡድኖች ለምኖና ተማጽኖ ነፃነትን ማግኘት ስለማይቻል የተነጠቅነውን ነፃነታችንን የምናስመልሰው ከምር በመታገል ብቻ ነው። ነፃነታችንን ዘረኞቹ ህወሃቶች የሚሰጡን እኛም የምንለምናቸው ሊሆን አይገባውም። ነፃነታችን የተፈጥሮ ስጦታችን ነው።ህወሃት አገራችን ያፈራቻቸው ነውረኛ ግለሰቦች ስብስብ ነው። እነዚህ ነውረኞች በዘረኝነት መጋራጃ ተጋርደው የነገውን ማየት ተስኗቸዋል።ከተጋረዱበት ዘረኝነት ወጥተው ዓይናቸውን ይገልጣሉ ማለትም አይቻልም። ያን ግዜና ሁኔታ ማለፋቸው ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯቸው ከዘረኝነት ውጪ ሌላ ህይወት ሌላ ፖለቲካ እንዳለ ማየት አያስችላቸውም። ያለን አማራጭ የተጋረዱበትን የዘረኝነት መጋረጃ አስገድዶ በመግለጥ ዓይናቸውን ከፍተው አርቀው እውነትን ማየት እንዲችሉ ማድረግ ነው።

 
Leave a comment

Posted by on October 11, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , , , , ,

አቶ ዓባይ ፀሐዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር፣ ሆነው ሊሰሩ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት ውስጥ ሊያደርግ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ (ቤልጂየም፣ ኔዘርላንድና ሉግዘንበርግ) አገሮች አምባሳደር ዶ/ር ካሱ ኢላላና በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ላይ መሆኑን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ 

በሚደረገው ዝውውር መሠረት አቶ ዓባይ ፀሐዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር፣ በአቶ ዓባይ ቦታ ደግሞ አቶ ሽፈራው ጃርሶ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ ዶ/ር ካሱን በመተካት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር ሆነው ወደ ብራሰልስ እንደሚዛወሩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

አምባሳደር ተሾመ ቶጋን በመተካት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የሚሾሙት ደግሞ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ነጋ ፀጋዬ መሆናቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡ 

አቶ ዓባይ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ፣ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት ይገነባሉ የተባሉትን አሥር የስኳር ፋብሪካዎችንና የሸንኮራ አገዳ ልማት በሚመለከት፣ ከተለያዩ የቻይና ኩባንያዎችና ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመነጋገርና በመስማማት ሥራውን ለማስጀመር ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ 

የሽንኮራ አገዳ ልማቱ በመስኖ መካሄድ ስላለበትና ለዚህ ደግሞ ባላቸው ዕውቀትና ልምድ ለሥራው ቅርብ ናቸው የሚባሉት የቀድሞው ውኃ ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በመሆናቸው፣ በአቶ ዓባይ ምትክ እንዲሾሙ ውሳኔ ላይ መደረሱን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ 

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱን በተባለው ፍጥነት በማቀላጠፍ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት በመዘግየቱ፣ አቶ ሽፈራው ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ በመጠቀም ሊያሳኩት ይችላሉ የሚል ግምት መያዙን ምንጮች አክለዋል፡፡ 

የባለሥልጣናት የሥራ ዝውውርና ሽግሽግ ሊቀጥል እንደሚችል ምንጮች ጠቁመው፣ የአራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የሚኒስቴር ዴኤታው ምደባ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይፋ ሊደረግ ይችላል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ኩማ ደመቅሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሲደረጉ፣ አሁን ደግሞ አቶ ዓባይ ፀሐዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላ ተጨምረዋል፡፡ 

source: ethiopian reporter

 
Leave a comment

Posted by on October 11, 2013 in AMHARIC

 

Tags: , , , , , , , ,